ሃሌሉያ ፡ አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተወለደ (Haleluya Amien Eyesus Tewelede) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሃሌሉያ አሜን ሃሌሉያ አሜን ሃሌሉያ አሜን

የሱስ ተወለደ በበረት የዓለምን ሀጢያት ሊያስወግድ

 

    ሰማይ ሰማያትን አልፍ ወረደ

ልጆቹን ለማዳን በበረት ተወለደ

እናከብረዋለን ያፈቀረንን

የዓለምን መድህን እየሱስን

 

    ጊዜና ዘመንን ቆጥሮና ጠብቆ

እኛ እንደ ደከመን እንደማችል አውቆ

እግዚአብሔርንና ሰውን ሊያገለግል

ተወለደ የሱስ በበረት ፍግ መሐል

 

    በሌጌዎን ጦር ላይ ሊያስመታ ነጋሪት

የዲያብሎስ ምሽግ ሀይሉን ሊያርበተብት

ተወለደ የሱስ በቤተልሔም

ሰላም ለዚህ ምድር ክብር በአርያም

 

    ከጎስቋላ ፊቱ ፍቅር የማይርቀው

የመስቀል አርበኛ እየሱስ ይሄ ነው

እንደ ወይን ጣዕም ሆኖ ኑሮህ እንዲጣፍጥ

 

የሰራዊት ጌታ እየሱስን ምረጥ


Navigation menu