የምሥራቹ ፡ ቃል (Yemeserachu Qal) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጌታህን ፡ አመስግን ፡ ክርስቲያን ፡ ተነሣ
ልብህን ፡ ከእጆችህ ፡ ጋር ፡ ወደ ፡ አምላክህ ፡ አንሣ
ኢየሱስ ፡ ተወልዷል ፡ የምሥራች ፡ ተናገር
እግዚአብሔር ፡ አምላክህን ፡ አመስግን ፡ በመዝሙር

አዝ፦ የምሥራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ በቤተልሔም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የአዋጅ ፡ ነጋሪ ፡ ድምፅ ፡ በምድር ፡ ሲያስተጋባ
የነቢያት ፡ ትንቢት ፡ ፍፁም ፡ ሳይዛባ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ መዳን ፡ ለሰው ፡ ሆኗል
ዕልል ፡ በል ! ተናገር ፡ የምሥራቹን ፡ ቃል

አዝ፦ የምሥራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ በቤተልሔም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የቀደመው ፡ አዳም ፡ ቢሞት ፡ በኃጥያቱ
አምላክ ፡ አልተወንም ፡ አልቆበት ፡ ምሕረቱ
አማኑኤል ፡ ተወልዷል ፡ ምድር ፡ ታስተጋባ
አመስግን ፡ በአፍህ ፡ በእጆችህ ፡ ጭብጨባ

አዝ፦ የምሥራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ በቤተልሔም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ በሥልጣን ፡ ሰባሪ
የንጋት ፡ ኮከብ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ አስከባሪ
እመን ፡ ትድናለህ ፡ ኢየሱስ ፡ ተወልዷል
ከዚያም ፡ አልፎ ፡ ተርፎ ፡ በበደልህ ፡ ሞቷል

አዝ፦ የምሥራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ በቤተልሔም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ


Navigation menu