ማን ፡ አለና (Man Alena) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በውድቅት ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ
ጌታን ፡ በእንጉርጉሮ ፡ ሳነሳ
መንገድም ፡ ሲጫወት ፡ ሳነሳሳ
የሚሞት ፡ ወደር ፡ የለህ

አዝ፦ ማን ፡ አለና ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ በቀር ፡ የሚከበር (፪x)

ስራመድ ፡ በመንገድ ፡ በጐዳና
የጌታን ፡ ማዳን ፡ አይ ፡ አስብና
እያዜምኩኝ ፡ ስጓዝ ፡ ለብቻዬ
መጠን ፡ አይኖረውም ፡ የደስታዬ

አዝ፦ ማን ፡ አለና ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ በቀር ፡ የሚከበር (፪x)

ባስብ ፡ ባስብ ፡ አጣሁ ፡ አለ ፡ ኢየሱስ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ሊወደስ
ዘወትር ፡ ከአፌ ፡ አይጠፋም ፡ በቅኔ
ሳመሰግንህ ፡ ነው ፡ በጉዞዬ

አዝ፦ ማን ፡ አለና ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ በቀር ፡ የሚከበር (፪x)

በዓለም ፡ አይደለም ፡ የማከብረው
የምስል ፡ አይደለም ፡ የማጌጠው
እኔም ፡ ሁሌም ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖልኛል
ስጠራው ፡ በልቤ ፡ ደስ ፡ ይለኛል

አዝ፦ ማን ፡ አለና ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ በቀር ፡ የሚከበር (፪x)

Navigation menu