ለፍቅር ፡ ትርጉም (Lefeqer Tergum) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)

ፍቅርን ፡ ሳስባት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ አልማለሁ
መላ ፡ አካላቴን ፡ አየዋለሁ
ፍቅሩ ፡ ሆን ፡ በውስጥ ፡ እረዳለሁ
የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)

ነፍስን ፡ ከመስጠት ፡ የበለጠ ፡ ነገር ፡ የለም
ይህችን ፡ ያህል ፡ ናት ፡ ፍቅር
ርህራሄ ፡ የሆነች ፡ ለዚህ ፡ ዓለም
ፍቅርን ፡ ለማየት ፡ ኢየሱስን ፡ መመልከት

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)

ከወደደን ፡ ልብ ፡ ወስጥ ፡ ያለች ፡ ፍቅር ፡ መፈፀሚቱ
የገለፀልን ፡ በሞቱ
ያልተለወጠች ፡ በመስዋዕቱ
ፍቅርን ፡ ለመቅመስ ፡ በኢየሱስ ፡ መታደስ

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)


Navigation menu