እንባዬን ፡ አፈሳለሁ (Enbayien Afesalehu) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በሥጋና ፡ በነፍስ ፡ ላይ ፡ ለሚሆን ፡ ፈተና
ሁሉንም ፡ የሚያስችለኝ ፡ መንፈስ ፡ ስጠኝና
እንደፈቀድክ ፡ አድርገኝ ፡ ሕይወቴን ፡ እመናት
ብትወድ ፡ ላመስግንህ ፡ ቢከፋኝም ፡ ላልቅስ

አዝ፦ በክብር ፡ ፀባዖቱ ፡ ገናናው ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ካለው
ፅዋዬም ፡ በፊትህ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ሳየው
እንባዬን ፡ አፈሳለሁ ፡ በምሥጋናም ፡ በለቅሶም
አምላኬ ፡ በቃህ ፡ እስኪለኝ ፡ ዓይኖቼን ፡ አብሶ

የእንባ ፡ ወንዛ ፡ ወንዝ ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ እያልኩ
ዳዊት ፡ በምሥጋና ፡ ሲስቅ ፡ ሲመላለስ
ሁሉን ፡ እንዳመሉ ፡ ጌታ ፡ ችለኸዋል
ባለቅስም ፡ ብስቅ ፡ አቅሜን ፡ አውቀኸዋል

አዝ፦ በክብር ፡ ፀባዖቱ ፡ ገናናው ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ካለው
ፅዋዬም ፡ በፊትህ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ሳየው
እንባዬን ፡ አፈሳለሁ ፡ በምሥጋናም ፡ በለቅሶም
አምላኬ ፡ በቃህ ፡ እስኪለኝ ፡ ዓይኖቼን ፡ አብሶ

ሊመጣ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ይህን ፡ ሳወዳድር
የምሥጋናዬንም ፡ የለቅሶዬም ፡ ዝርዝር
እኩያ ፡ የለውም ፡ ምጻቱ ፡ የሚለው
ሁሉን ፡ አየዋለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲመለስ

አዝ፦ በክብር ፡ ፀባዖቱ ፡ ገናናው ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ካለው
ፅዋዬም ፡ በፊትህ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ሳየው
እንባዬን ፡ አፈሳለሁ ፡ በምሥጋናም ፡ በለቅሶም
አምላኬ ፡ በቃህ ፡ እስኪለኝ ፡ ዓይኖቼን ፡ አብሶ

ከአካል ፡ ሰው ፡ እንዳልሮጥ ፡ ዘመን ፡ ገፋ ፡ ብዬ
ማስተዋልህ ፡ ጐሎት ፡ የሥጋ ፡ አእምሮዬ
በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰንከው ፡ ቦታ
ፈቃድህን ፡ እንዳውቅ ፡ እምነቴን ፡ አበርታ

አዝ፦ በክብር ፡ ፀባዖቱ ፡ ገናናው ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ካለው
ፅዋዬም ፡ በፊትህ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ሳየው
እንባዬን ፡ አፈሳለሁ ፡ በምሥጋናም ፡ በለቅሶም
አምላኬ ፡ በቃህ ፡ እስኪለኝ ፡ ዓይኖቼን ፡ አብሶ


Navigation menu