በመዝሙር ፡ ውዳሴ (Bemezmur Wedasie) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 1.jpg


(1)

እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው
(Endiet Denq Amlak New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ቀናትም ፡ ያልፉና ፡ ዘመን ፡ ተፈፅሞ
የክርስቲያን ፡ ፈተና ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አክትሞ
በጥፋት ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ መኖር ፡ ያበቃና
የዓይናችንን ፡ እንባ ፡ ጌታም ፡ ይጠርግና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና

መች ፡ ይላል ፡ ተመሥገን ፡ ጊዜው ፡ ይደርስና
ከልቡ ፡ አልቅሶ ፡ ለጌታው ፡ ይነግርና
ምኞቱም ፡ ጥረቱም ፡ መቼ ፡ ይሳካና
ጌታን ፡ ሲል ፡ ይሰማል ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ተፅናና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና

አእላፋት ፡ ፃድቃን ፡ ከምድር ፡ እንሄድና
ነጭ ፡ ልብሳችን ፡ ለብሰን ፡ ዙፋን ፡ እንከብና
ኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ ለበጉ ፡ እንሰግድና
መች ፡ እንዘምር ፡ ይሆን ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና

የምድር ፡ መፃተኛ ፡ ልብህ ፡ የተሰቀለ
ሰማያትን ፡ ለማየት ፡ ተስፋ ፡ ያልጐደለህ
መቼ ፡ ቀን ፡ ሞልቶልን ፡ ፅዮን ፡ ትደርስና
ጌታን ፡ በዓይንህ ፡ አይተህ ፡ ልብህ ፡ ይረካና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና