የማይዘለቅ ፡ ሰላም ፡ አለኝ (Yemayezeleq Selam Alegn) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የማይዘለቅ ሰላም አለኝ

የተትረፈተፈ ህይወት አለኝ

ነፍሴ ለመለመች የሱስን ካመነች

 

    ቅብዝብዝ ኑሮ የጨለማ

በዓለም ኃጢያአት የተግማማ

እንደ እርጎ ረጋ ጣፍጦ

በኢየሱስ ተለውጦ (2)

 

    የጥንቱ ህይወቴ ያመራራ

ጣዕም ያልነበረው እንደ ማራ

እንደ እርጎ ረጋ ጣፍጦ

በየሱስ ተለውጦ (2)

 

    እርካታ የለው ጭፍን ኑሮ

የቀድሞው ቤቴ የዕሮሮ

እንደ እርጎ ረጋ ጣፍጦ

በየሱስ ተለውጦ (2)

 

    ዓላማ ሳይኖር የባዘነው

ከንቱ ምኞቴ የቀደመው

እንደ እርጎ ረጋ ጣፍጦ

 

በየሱስ ተለውጦ (2)


Navigation menu