የማይረታ ፡ ነው (Yemayereta New) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የማይረታ ነው የማይረታ

የማይረታ ነው የሱስ

የጠላትን ኃይል የሚያፈራርስ

የማይረታ ነው የኛ ጌታ የሱስ

 

    ጠላት ከቦን ሳለ ሊውጠን በቃ አከተመልን ብለን

ሞት በላያችን አንጃቦ ሕይወት በፍርሃት ተከቦ

ይመስገነው ድል አገኘን ጌታ ቀንበሩን ሰበረልን

የድል አምላክ አለን

 

    ትዕግስት አልቆ ሳለ ሆድ ብሶን የፀሎት መልስም ጠፍቶብን

ፈጥኖ ጌታችን ደረስ ሃዘንተኛውን ዳሰሰ

ይመስገነው አድሶናል ዳግም በሙላት ጎብኝቶናል

ድልን አልብሶናል

 

    እኛን በጠላት ውስጥ ከቶን የጣር ጭንቀት ጩኸት ከቦን

ጥሎን የሚሄድ በትኖን አይደለም ያከብራል ቃሉን

ይመስገነው ጌታ አፀናን አይረታም የሱስ ጌታችን

 

የድል ፅዋ አጠጣን


Navigation menu