የአምላክ ፡ ልጆች ፡ ምሥጋና (Yeamlak Lejoch Mesgana) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እንደ ጥንት ጊዜ እንደ ሃዋርያት እለት እለት አዳዲስ ነፍሳት

      በዳነው ላይ እየጨመረ ኢየሱስ በፍቅር ከበረ

      የእኛም ደስታ ይኸውና እልል እንበል በምስጋና

 

የአምላክ ልጆች ምስጋና አምጡ

 ነፍሳት ከሲኦል አመለጡ

የእግዚአብሔር በዝቷል ቸርነቱ

ዝም አትበሉ ምስጋና አምጡ

 

    የምሬት የሃዘን የእምባ ጉዞ ይጓዝ የነበር ሞት አርግዞ

      ዛሬ በየሱስ ተፈታና ደስ ብሎት ቆመ በምስጋና

      የጽድቅ ፀሐይ በርቶለታል እግዚአብሔር በርሱ ደስ ብሎታል

 

    የእስራት ኑሮ በቅቷልና ለዚህ ቤት መዳን ሆኗልና

      እኛም ሃሴት እናድርግ አብረን ነፍሳት ሲድኑ ስላሳየን

      ለአምላካችን እንዘምር እያልን ይሁን ለእግዚአብሔር ክብር

 

    በረት የተወለደው የሱስ አምሳያ የለሌለው ፍጹም ቅዱስ

      ዛሬም በሰው ልብ ተወለደ ከጥፋት ሊያድነው ወደደ

      የአምላክ ልጆች እንደገና እልል እንበል በምስጋና

 

    በላይ በሰማይ ታላቅ ደስታ አንዲትን ነፍስ ሲታደግ ጌታ

      መላዕክት በሰማይ እልል አሉ ከጥፋት የዳነውን ሲያዩ

 

      እኛም በምድር እንዘምር እያስተዋልነው ይህን ሚስጥር


Navigation menu