ዋጋ ፡ ያስከፍላልና (Waga Yaskefelalena) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የቀድሞ ነቢያትና ሐዋርያት ደምና እንባ

      ታስቦ በፊትህ ዋጋ አግኝቷልና አባባ

      ዛሬም በእምነት ቆሜ እጠብቅሃለሁ

      ዋጋ ከፍዬበት አክሊሌን እወስዳለሁ

 

ዋጋ ያስከፍላልና ክርስትና ገና ምኑ ተያዘና

የአባቶቼን ወግ አይቼ የነቢያትና የሐዋርያትን ፅዋ ጠጥቼ

ሽልማቴን እቀበላለሁ ገና ዋጋ እከፍላለሁ

 

 

    ዋጋ ያስከፍላል ከየሱስ ጋር ኑሮ

      በዓለም ተሰዶ ተጎሳቁሎና ተባሮ

      የህይወትን አክሊል ለመቀበል

      ላለፉት ለእኔም ዋጋ ያስከፍላል

 

    የፅድቅና የድል አክሊል በላይ ተዘጋጅቶ

       ከጌታ ልቀበል በወንጌል እምነቴም ፀንቶ

       በእግር ግንድ እስራት ተጨንቄ

       ብድራቴን ከእጁ ወስዳለሁ ጠብቄ

 

    በድንጋይ ውግራት በመጋዝም ተሰንጥቄ

       በዘይት ቅቅላት በአንበሳ አፍ ተነጥቄ

       ሽልማቴም የክብር አክሊል ነው

 

       ካምላክ እጅ ልቀበል ጊዜያቱ ቅርብ ነው


Navigation menu