ጸሎቴን ፡ የሰማልኝን (Tselotien Yesemalegnen) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ፀሎቴን የሰማልኝን

 ፈጥኖም የደረሰልኝን

እንደ ታናሽነቴ ያልናቀኝን

እግዚአብሔርን እስኪ ላመስግነው (2)

 

    በእርጋታ ተቀመጥ ቁጭ ብለህ አድምጠኝ

ለመከራ አትስጋ ልብህን ጣልብኝ

       ብሎ የመከረኝን አምላኬን ሰምቼ

       መልስን አግኝቻለሁ በፊቱ ቆይቼ

 

    እንደ አጥር ዙሪያዬን ከከበበኝ ጠላት

      ረድኤት ተልኮ ከልዑል ዙፋን ፊት

      ነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ በተነው

      ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ቀላል ነው

 

    ምርኮዬን መልሶ ደስተኛ አረገኝ

       በሃዘኔ አጽናንቶ ከጎኔ ቆመልኝ

       እንደገና አዲሱን ህይወት ላስጀመረኝ

       የናዝሬቱን የሱስ ተመስገን በሉልኝ

 

    ጸድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ቢሸሽገው

      የእግዚአብሔር ስም የጸና ግንብ ነው

      የችግረኛውን ጸሎት የሚመልስ

 

      እንደ እግዚአብሔር የለም እሰከ ዛሬ ድረስ


Navigation menu