ምህረትህን ፡ ልየው (Meheretehen Leyew) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምህረትህን ልየው (2) ማዳንህን ልየው በምድሬ

ምህረትህን ልየው (2) ኦ ክንድህን ልየው በአገሬ

 

    ያቤፅን የሰማህ ሲማጸን ሃገሩን ያሰፋህ ድንበሩን

      እኔም በፊትህ እጮሃለሁ ምድሬን እንድታስብ እሻለሁ

 

    የባዕድ መሰዊያ ስታፈርስ መንፈስህ በምድሬ ላይ ሲፈስ

      የጠላትን ደጅ እንደቃልህ ስታወርሰኝ ጌታ ሆይ ልይህ

 

    ሕዝብህን የማጥፋት ምኞቱን የአጋንንት የደም ጥማቱን

      ቤትህን ለማርከስ ያሰበው ከንቱ ይሁን ጌታ ቅደመው

 

    የጠፉትን ነፍሳት ስትመልስ የአጋንንትን ሥራ ስታፈርስ

       በሰማይ በምድር በረከት ኢትዮጵያን ስትጎበኝ ልመልከት

 

    በዘመኔ ጌታ ክብርህን ስትፈጽም የተስፋ ቃልህን

 

      ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ስትታሰብ ልያት ኦ ጌታ


Navigation menu