Kefa Mideksa/Hulu Beju New/Qedus Egziabhier

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ኬፋ ሚደቅሳ ሌላ ሥም ቁፋ ሚዴቅሳ ርዕስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው አልበም ሁሉ በእጁ ነው

ቅዱስ እግዚአብሔር ያለ የነበርከው አንተ እኮ ነህ ለእኔ ከለላ የሆንከው (፬x)

ሌላማ ምን እከፍልሃለሁ ምሥጋና በፊትህ እሰዋለሁ (፪x)

አንተ እኮ ነህ በሕይወት እንድኖር ያደረከኝ ከዚያ ከጨለማ ከሞት የታደከኝ ስለ እኔ የቆሰልከው የደቀቀከው ጌታ በልቤ ይኖራል የአንተ ውለታ (፪x)

ይገርመኛል ከሞት መትረፌ ይገርመኛል በአንተ መታቀፌ ይገርመኛል ቸሩ የእኔ ጌታ ይገርመኛል ሆንክልኝ መከታ (፫x)

በረሃብ ዘመን ጥጋብ ሲሆንልኝ ያዩ ዛሬ ከእኔ ጋራ አንተን ያመልካሉ እኔም በመደነቅ በመገረም ሆኜ አመልክሃለሁኝ በመቅደስህ ቆሜ (፪x)

ይገርመኛል ከሞት መትረፌ ይገርመኛል በአንተ መታቀፌ ይገርመኛል ቸሩ የእኔ ጌታ ይገርመኛል ሆንክልኝ መከታ (፫x)