ከልኩ ፡ አያልፍም (Keliku Ayalfim) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ካሳሁን ፡ ለማ
(Kasahun Lema)

Kasahun Lema 1.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው
(Egziabhier Qen Alew)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kasahun Lema)

"ወይ ፡ የምታልፍ ፡ ብሎ ፡ ያለወትሮው ፡ ሞልቶ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ቢፎክር ፡ ቢቆምም ፡ ከፊቴ
በዳር ፡ አስከ ፡ ክብር ፡ እሄዳለሁ ፡ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
ረግጬው ፡ አልፋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፣ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ"


አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም
የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x)
ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x)
 
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ብያነድ ፡ ጠላቴ ፡ እሳቱን ፡ አብዝቶ
ከከፍታዬ ፡ ላይ ፡ አልወርድም ፡ ስፍራ ፡ አለቅም ፡ ከቶ
የመቆሜ ፡ ሚስጥር ፡ ጌታ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ ሁኔታ
የታመንኩበትን ፡ አውቃለሁ ፡ አንደማይረታ (፪x)
 
አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም
የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x)
ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x)

ጠላቴን ፡ ከፊቴ ፡ አውጥቶት ፡ አጥፋው ፡ ብሎ ፡ አዞኛል
አስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ ሰብሮልኛል
የከፍተኛነቴ ፡ ሰይፍ ፡ ብቃቴም ፡ እርሱ ፡ ነው
አትፍራ ፡ ሰላለኝ ፡ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው(፬x)

አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም
የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x)
ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x)
 
ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ አስደንቆኛል (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ስራዬን ፡ ሁሉ ፡ ሰርቶልናል (፪x)
ላመስግነው ፡ አንጂ ፡ ስሙን ፡ በዝማሬ (፪x)
ለጠላቴ ፡ ሃዘን ፡ የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፣ የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ (፪x)

አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም
የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x)
ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፱x)


Navigation menu