እልፍ ፡ ቃል ፡ በኖረኝ (Elf Qal Benoregn) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ካሳሁን ፡ ለማ
(Kasahun Lema)

Kasahun Lema 1.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው
(Egziabhier Qen Alew)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kasahun Lema)

ኢየሱስ ፡ አለቴ ፡ ነህ ፡ ተደግፌሃለሁ
አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ ፡ በጥላህ ፡ አርፋለሁ
ከቶ ፡ አልጨነቅም ፡ ለነገዬ ፡ ብዬ
ሁሉን ፡ የምትሆን ፡ ስላለህ ፡ ጌታዬ
ሁሉን ፡ የምትሆን ፡ ስላለህ ፡ ጌታዬ (፪x)

አዝ፦ እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢኖረኝ ፡ አንተን ፡ ማሞገሻ (፪x)
አመስግኜ ፡ አልጠግብም ፡ እስከመጨረሻ (፪x)

ባለ ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ባለ ፡ ብዙ ፡ ፀጋ
ማንስ ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል ፡ አንተን ፡ የተጠጋ
በጊዜው ፡ የምትደርስ ፡ ተቀድመህ ፡ አታውቅም
ታማኝ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትዋሽም
ታማኝ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትዋሽም (፪x)

አዝ፦ እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢኖረኝ ፡ አንተን ፡ ማሞገሻ (፪x)
አመስግኜ ፡ አልጠግብም ፡ እስከመጨረሻ (፪x)

ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ለኔ ፡ ያለህ ፡ አላማ
ፍፁም ፡ ደግነትህ
(፪x)

ልትመለክ ፡ የሚገባህ
ልትወደስ ፡ የሚገባህ (፪x)

ገናና ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ
ከፍ ፡ በል ፡ በምድርም ፡ በሰማይ (፪x)

ብንሰግድልህ ፡ ብናመልክህ
ስለሚገባህ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ (፪x)

ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ (፰x)


Navigation menu