ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል (Weha Weha Endayel) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ
ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ፡ ሰጥተህ
መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ
መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ

ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ
ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ፡ ሰጥተህ (፪x)
መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ
መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ (፫x)
እንደገና ፡ አመልክሃለሁ
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ
እንደገና

ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ እስካሁን ፡ የባረከኝ
አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ ፡ ባርከኸኝ ፡ ባርከኸኝ (፪x)
ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ ራስህን ፡ የሰጠኸኝ
አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ ፡ ሰጠኸኝ ፡ ሰጠኸኝ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ (፫x)
እንደገና ፡ ሰጥሃለሁ
እንደገና ፡ ሰጥሃለሁ ፡ እንደገና

ገነት ፡ ገብቻለሁ ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ
አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x)
ገነቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ
እኔ ፡ አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ እንደገና
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ እንደገና

አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና
እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና
አመሰግናለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ እንደገና
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ እንደገና (፪x)


Navigation menu