ምርኩዜ (Merkuzie) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምርኩዜ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም ፣ አይደለም (፪x)
ምርኩዜ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም (፪x)

ይብላኝ ፡ አምላክ ፡ ለሌለው
መታመኛ ፡ የሚሆነው
እኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
እሚያስተማምነኝ (፪x)

በምንም ፡ ተዓምር ፡ አላቋርጥም
በአንተ ፡ መመካቴ ፡ እኔ ፡ አላቆምም (፪x)
ምርኩዝዬ ፡ አንተ ፡ ታስፈልገኛለህ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እኔን ፡ ታቆማለህ (፪x)

ይብላኝ ፡ ይብላኝለት ፣ ይብላኝለት
አምላክ ፡ ለሌለው (፪x)

እኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ እሚያስተማምነኝ
እኔስ ፡ አባት ፡ አለኝ ፡ አይዞሽ ፡ ልጄ ፡ ይለኝ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ አለኝ ፡ እሚያስተማምነኝ

በምንም ፡ ተዓምር ፡ አላቆምም
በአንተ ፡ መመካቴ ፡ እኔ ፡ አላቋርጥም (፪x)
ምርኩዝዬ ፡ አንተ ፡ ታስፈልገኛለህ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ታዛልቀኛለህ (፪x)

ምርኩዜ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም ፡ (አይደለም) (፪x)
ምርኩዜ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም ፡ (አይደለም) (፪x)
ምርኩዜ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም (፪x)

ይብላኝ ፡ አምላክ ፡ ለሌለው ፡ መታመኛ ፡ የሚሆነው
እኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ እሚያስተማምነኝ (፪x)

ይብላኝ ፡ ይብላኝለት ፣ ይብላኝለት
ኢየሱስ/አዳኝ ፡ ለሌለው (፪x)

እኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ ፡ ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ
እኔስ ፡ አዳኝ ፡ አለኝ ፡ ጉልበቱን ፡ የሰጠኝ
እኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ ፡ ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ

ምርኩዝህ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም ፡ (አይደለም) (፪x)
ምርኩዝሽ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም ፡ (አይደለም) (፪x)
አይደለም ፡ (አይደለም) (፬x)
ምርኩዝህ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም
ምርኩዝሽ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለም
አይደለም (፰x)


Navigation menu