ሃሌሉያ (Hallelujah) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x)

ሕይወቴን ፡ በእጁ ፡ የያዘ ፡ መንገዴን ፡ የሚቀይሰው
አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነዉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነዉ
ሕይወቴን ፡ ሰጥቸዋለሁ ፡ መልሼ ፡ ከእጁ ፡ አልወስደዉም
ከእንግዲህ ፡ ሕይወት ፡ የለኝም ፡ ሕይወቴ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነዉ

አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x)

አረጋግጣለሁ ፡ በከንፈሬ ፡ ቃል
በልቤ ፡ በሃሳቤ ፡ መቼ ፡ ይርቃል
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ ፍቅሬን ፡ አዉጃለሁ
እኔ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነኝ ፡ እወቁት ፡ እላለሁ (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x)

የገባዉ ፡ ሰዉ ፡ በአንተ ፡ መታየቱ
መወደዱ ፡ ደህንነት ፡ ማግኘቱ
ሳይለመን ፡ ሁሌ ፡ ያመልክሃል
በአንደበቱ ፡ ክብርን ፡ ይሰጥሃል (፪x)

አረጋግጣለሁ ፡ በከንፈሬ ፡ ቃል
በልቤ ፡ በሃሳቤ ፡ መቼ ፡ ይርቃል
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ ፍቅሬን ፡ አዉጃለሁ
እኔ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነኝ ፡ እወቁት ፡ እላለሁ (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x)

የገባዉ ፡ ሰዉ ፡ በአንተ ፡ መታየቱ
መወደዱ ፡ ደህንነት ፡ ማግኘቱ
ሳይለመን ፡ ሁሌ ፡ ያመልክሃል
በአንደበቱ ፡ ክብርን ፡ ይሰጥሃል (፪x)


Navigation menu