ነፍሴን ፡ የሚያረካ (Nefsien Yemiyareka) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ነፍሴን ፡ የሚያረካት
አምላክ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ናና ፡ በመገኘትህ ፡ አርካት
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ነፍሴን ፡ የሚያረካት
አምላክ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ናና ፡ በመገኘትህ ፡ አርካት (፭x)

አንዳንዶች ፡ ገንዘብ ፡ ይላሉ
አንዳንዶች ፡ ዝና ፡ ይላሉ
አንዳንዶች ፡ ዘመድ ፡ ይላሉ
አንዳንዶች ፡ ዕውቀት ፡ ይላሉ
እኔ ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ
አንተው ፡ ነህ ፡ የምትበልጠው (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ
ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪x)

ብርና ፡ ወርቅ ፡ አያጓጓኝም
ልቤን ፡ አይነካኝም ፡ ዓይኔን ፡ አይስበኝም
የሚያጓጓኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ነው
ርሃቤ ፡ ጥማቴ ፡ ጽድቁ ፡ ነው ፡ ጽድቁ ፡ ነው (፪x)

አንተን ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የተጠማችው
አንተን ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የተመኘችው
የአንተን ፡ ስጦታ ፡ መፈለግ ፡ ትታለች
አንተን ፡ እራህን ፡ ትፈልጋለች
የአንተን ፡ በረከት ፡ መፈለግ ፡ ትታለች
አንተን ፡ ራስህን ፡ ትፈልግሃለች

ምን ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አለ
ከዚህ ፡ ፀሐይ ፡ በታች
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ እንጂ
ለሰዎች ፡ የሚበጅ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለሰዎች ፡ የሚበጅ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ
ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪x)

መዝገቤ ፡ እኮ ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ነው
መዝገቤ ፡ በሰማይ
መዝገቤ ፡ በአለበት
ልቤስ ፡ በዚያ ፡ አይደል ፡ ወይ (፫x)

ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ
ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ


Navigation menu