እኔእንጃ (Enienja) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እኔ ፡ እንጃ (፪x) ፡ ቃል ፡ አገኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ
ለመግለጽ ፡ የሚሰማኝን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስሆን (፪x)

ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት
ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት
ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
እግዚአብሔር ፡ ያለበት (፬x)

የእግዚአብሔር ፡ መንግስት ፡ ጽድቅና ፡ ሰላም
በመንፈስ ፡ የሆነ ፡ ደስታ ፡ ናት (፬x)
ጸጥታ ፡ ያለበት ፡ እረፍት ፡ የሞላበት
እፎይታ ፡ ያለበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት

ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት
ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
እግዚአብሔር ፡ ያለበት (፬x)

እኔ ፡ እንጃ (፪x) ፡ ቃል ፡ አገኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ
ለመግለጽ ፡ የሚሰማኝን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስሆን (፪x)

አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኛማ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)
አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፬x)
የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
የእኔ ፡ አምላክ ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር

ሥጋዬን ፡ አልነጭም ፡ ፊቴን ፡ አልቧጭርም
አምላኬን ፡ ለማግኘት ፡ ብዙ ፡ አልቸገርም
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለው ፡ አቤት ፡ የሚለኝ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ያለኝ

የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
የእኔ ፡ አምላክ ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
የሚናገር ፡ የሚናገር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ
የሚናገር ፡ የሚናገር ፡ የሚነግረኝ ፡ የሚነግረኝ
የሚያወራኝ ፡ የሚያወራኝ

አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፬x)
አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፮x)


Navigation menu