Kalkidan Tilahun/Atelewawetem/Amelkalehu Yehen Negus

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ አመልካለሁ አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ንጉሥ ፡ አመልካለሁ አመልካለሁ ፡ አመልካለሁ (፬x)

አንድና ፡ ብቸኛ ፡ የሌለው ፡ ጓደኛ (፪x)
ተቀናቃኝ ፡ የለው ፡ የሚፎካከረው
ከዘመናት ፡ መሃል ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ነው (፪x)

እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፣ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ሳይነዋወጥ ፡ እስካሁን ፡ ያለው (፪x)

ሳይነዋወጥ ፡ እስካሁን ፡ ያለው (፪x)

አንድና ፡ ብቸኛ ፡ የሌለው ፡ ጓደኛ (፪x)
ተቀናቃኝ ፡ የለው ፡ የሚፎካከረው
ከዘመናት ፡ መሃል ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ነው (፪x)

የተቆጠቆጠ ፡ በክብር ፡ ክብር ፡ ክብር የተጥለቀለቀ ፡ በሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር (፪x) ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ (፪x)

እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፣ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
እስካሁን ፡ ድረስ ፡ በክብር ፡ ያለው (፪x)
በክብር ፡ ያለው ፣ በክብር ፡ ያለው
በሞገስ ፡ ያለው ፣ በሞገስ ፡ ያለው (፪x)

ሠማያትን ፡ የሚነቀንቀው ፡ ምድርንም ፡ የሚጠቀልለው ሠማያትን ፡ የሚነቀንቀው ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አምላክ ፡ አለ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ንጉሥ ፡ አለ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፣ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሳይነዋወጥ ፡ እስካሁን ፡ ያለው (፪x)

አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ አመልካለሁ አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ንጉሥ ፡ አመልካለሁ አመልካለሁ ፡ አመልካለሁ (፬x)