አግዘኝ (Agezegn) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

hannh

ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
ለውድቀት ፡ መሮጤ ፡ ምንድነው
ማዳንህ ፡ የገባኝ ፡ ጥንት ፡ ነው
አባቴ ፡ ልጄ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ እያልከኝ
የጎረቤት ፡ ኑሮ ፡ የናፈቀኝ
ጥፋቱ ፡ ከጠላት ፡ ወይ ፡ ከኔ
ገብቶኝ ፡ እንዳልገባው ፡ መሆኔ
አመል ፡ ካልሆነብኝ ፡ በስተቀር
አሁን ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ጠላት ፡ ሰፈር

አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x)

ማን ፡ አየኝ ፡ አላየኝ ፡ ኑሮዬን
አልደብቀው ፡ ካንተ ፡ ገበናዬን
ሰው ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ሸሽቶስ ፡ እስከመቼ
ልኑር ፡ መጀመሪያ ፡ አንተን ፡ ፈርቼ
እንዳልሞት ፡ ነበረ ፡ መዳኔ
ፈቅደህ ፡ የሞትክልኝ ፡ ካህኔ
እያወቅኩ ፡ ከገባሁ ፡ ከእሳቱ
ማን ፡ ሊመልሰኝ ፡ ነው ፡ ማን ፡ ብርቱ

አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x)

ነጻነቴም ፡ በዛ ፡ መሰለኝ
ምን ፡ አለበት ፡ ኑሮ ፡ ለመደኝ
ቀለለኝ ፡ የጥፋት ፡ መንገዴ
ላይቀርልኝ ፡ ካለፈ ፡ መንደዴ
የማውቀውን ፡ እውነት ፡ ሳልገፋ
ከበር ፡ መልስ ፡ ሳልሆን ፡ ሳልጠፋ
ብላቴናነቴን ፡ ታደገው
አውለው ፡ ከቤትህ ፡ ከሚበጀው

አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ (ደግፈኝ)
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ (ብቻዬን----አቅም ፡ የለኝ)
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር (ያየህልኝን----ቁም ፡ ነገር)
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (እንዳላጣው----ተራ ፡ ነገር) (፪x)