ክንደ ፡ ብርቱ (Kende Bertu) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
አበቃ ፡ አከተመ ፡ አይሆንም ፡ በተባለበት
የጌታ ፡ ስም ፡ ሲጠራ ፡ ሁሉ ፡ ይዘራል ፡ ህይወት
ያለአንዳች ፡ እርዳታ ፡ ብቻውን ፡ ድንቅን ፡ አድርጐ
ልጆቹን ፡ ያሣርፋል ፡ በሀይሉ ፡ ተገለጦ
ታላቅነቱ ፡ አይወሰን ፡ ከ ፡ እስከ ፡ አይባልም
ብቻ ፡ እርሱ ፡ ይስራ ፡ እንጂ ፡ ማንም ፡ ፊቱ ፡ አይቆምም
(፪x)

አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)

ጽኑ ፡ ግንብ ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ የማይደፈር ፡ መከታ
ከክፋት ፡ ከሰይጣን ፡ እጅ ፡ የሚከልል ፡ ጌታ
ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ ሀይለኛና ፡ ባለስልጣን
ተጠግተነው ፡ አርፈናል ፡ መደገፊያ ፡ ሆኖልን
ጥበቃው ፡ እጅግ ፡ ያስደንቃል ፡ ልጆቹን ፡ ያሳርፋል
ሀይሉም ፡ ከቶ ፡ አይደክምም ፡ በሰልፍ ፡ ይበረታል
(፪x)

አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)

ጌታ ፡ ከርሱ ፡ ጋር ፡ የሆነ ፡ ኽረ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻዋል
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ ሆኖ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
በክፉ ፡ ቀን ፡ አይሰጋም ፡ አምላኩ ፡ ይታደገዋል
ከረግረግ ፡ ከጭቃ ፡ አውጥቶ ፡ በአለት ፡ ያቆመዋል
ዛሬም ፡ ይህ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ ምንደነው ፡ የሚያስፈራን
በእርሱ ፡ እየተማመንን ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
(፪x)

አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)

ከጌታ ፡ የተነሳ ፡ በህይወት ፡ መኖር ፡ ችለናል
ካስጨናቂዎቻችን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርፈናል
ማዳኑን ፡ የክንዱን ፡ ብርታት ፡ ባይናችን ፡ አሣይቶናል
ስለዚህም ፡ ልናከብረው ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ መጥተናል
ለክበሩ ፡ እንዘምራለን ፡ እናመሰግነዋለን
ጌታ ፡ ስለሚገባው ፡ እናመልከዋለን
(፪x)

ምስጋና ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፫x)
ሌላ ፡ ምን ፡ ይሰጠዋል ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፬x)