Getayawkal and Birucktawit/Meder Alefelat/Yehie New Egziabhier

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ጌታያውቃል ግርማይ እና ብሩክታዊት አሰፋ ርዕስ ይሄ ነው እግዚአብሔር አልበም ምድር አለፈላት

አዝ ይሄ ነው እግዚአብሔር ለእኔ የደረሰው ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው ስለዚህ በፊቱ ምሥጋናን እሰዋለሁ ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ (፪x)

ምን እላለሁ ምሥጋና ለእርሱ ሰጣለሁ ምን እላለሁ ምሥጋና አበዛለሁ (፪x)

ፀሐይ ምትወጣ በስተምስራቅ በኩል ሲመሽባት ደግሞ በስተምዕራብ ብትሆን ማንም አይገረምም በነዚህ ድርጊቷ ወግና ስርአቷ ልክ ከጥንት ፍጥረቷ አንድ ቀን በደቡብ ብትወጣ በድንገት ሲመሽባት ደግሞ ሰሜንን ብትመርጥ ያኔ እንግዳ ነገር ለሁሉም ይሆናል ለእኔ ግን አምላኬ ከዚህ በላይ አድርጓል

ጉድ ተባለ ሆኖ ያልተጠበቀ ተሰራልኝ በዓለም ያልታወቀ እርሱ ሚለው የመዳኔ ነገር ከሞት የመትረፌ አያልቅም ቢነገር (፬x)

አዝ ይሄ ነው እግዚአብሔር ለእኔ የደረሰው ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው ስለዚህ በፊቱ ምሥጋናን እሰዋለሁ ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምሥጋና ለእርሱ ሰጣለሁ ምን እላለሁ ምሥጋና አበዛለሁ (፪x)

እንዲህ በቀላሉ እንደዋዛ ታልፎ ሊተው አይቻልም አያስቀምጥ አርፎ ውስጡ የተቀመጠው ምህረቱ የገባው ይነዘንዘዋል ቀን ከሌት ውለታው ቢያቅተኝ ቢቸግረኝ ዝም ማለት ጉባኤ መጣሁኝ ሕዝቡ ባለበት እኔ እያስታወስኩኝ ያረገውን ስራ አምልኮን ልሰዋ ከጉባኤው ጋራ

የገባው ሰው የተደረገለት ያላስቻለው ውለታው ያለበት ይነሳና አብሮኝ ከፍ ያድርገው ምህረትና ፍቅር እሰከ ዘለዓለም ነው (፬x)

አዝ፦ ይሄ ነው እግዚአብሔር ለእኔ የደረሰው ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው ስለዚህ በፊቱ ምሥጋናን እሰዋለሁ ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምሥጋና ለእርሱ ሰጣለሁ ምን እላለሁ ምሥጋና አበዛለሁ (፪x)

በመስቀል ላይ ለእኔ የሰራውን ስራ ቀንም ሆነ ሌሊት ሁልጊዜ ባወራ ቃላት አይበቃኝም ዓረፍተ ነገሮች እንጂ የእርሱ ስራ አያልቅም እንደ ሌሎች ዕልልታና አምልኮ ላምላኬ ሳላስቀር በምሥጋና ፊቱ ከመቅረብ በስተቀር ሌላ ምን ምርጫ አለኝ ለእርሱ የምሰጠው ገና ጨማምሬ ምሥጋና እሰዋለሁ

መቼ ያልቃል ቢወራ ቢወራ ተናግሬ መቼም አያበቃ እርሱም ቢሆን የመዳኔ ነገር የመስቀሉ ስራ አያልቅም ቢነገር (፬x) የኢየሱስ ስራ አያልቅም ቢነገር (፪x)

አዝ፦ ይሄ ነው እግዚአብሔር ለእኔ የደረሰው ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው ስለዚህ በፊቱ ምሥጋናን እሰዋለሁ ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምሥጋና ለእርሱ ሰጣለሁ ምን እላለሁ ምሥጋና አበዛለሁ (፪x)

"ጸሎት ሰዓት"

አዝ፦ አተገመትም በሊቃናት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (፪x)

የችግር ቋጠሮ ውስብስብ ሲልብኝ መግቢያ መውጫ ጠፍቶህ ግራ ሲያጋባኝ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ደግሞ ሲፈታታ ችግር ሁሉ ሲተን የትላንት ጨለማ እንደጉም ሲበተን አንተ ከሁሉ በላይ ነህ

አዝ፦ አተገመትም በሊቃናት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ/ (፪x)

አንተን እንዳላመልክ ከፍታው ዝቅታ ከቶ አያግደኝም አይጠፋኝ ዕልልታ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ውስጤ ቅኔ ሞልቷል ከገጠመኝ በላይ አምላኬ እግዚአብሔር ነህና ኤልሻዳይ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ

አዝ፦ አተገመትም በሊቃናት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (፪x)

ሁሉም ነገር ጠፍቶ በቤቴ የሚበላ ያልጠበኩት ነገር ሲሆንብኝ ሌላ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ደግሞ በጐጆዬ በረከት ሲሞላ ሁሉም ነገር ሞልቶ ሲተርፈኝ ለሌላ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ

አዝ፦ አተገመትም በሊቃናት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (፪x)

ሲሞላ ዘምሬ ሲጐድል ላላለቅስ በምንም ሁኔታ አምልኮ አልቀንስ አንተ ከሁሉም በላይ ነህ እታመንሃለሁ በምሥጋና ሆኜ ድል እንደምትሰጠኝ በስምህ አምኜ አንተ ከሁሉም በላይ ነህ

አዝ፦ አተገመትም በሊቃናት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (፪x)