Getayawkal and Birucktawit/Meder Alefelat/Mesgana

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ጌታያውቃል ግርማይ እና ብሩክታዊት አሰፋ ርዕስ ምሥጋና አልበም ምድር አለፈላት

አዝ በማለዳ ምሥጋናዬን አበዛለሁ፣ በቀትርም ሌላ ክብር እጨምራለሁ። ጊዜው መምሸቱ ውድቅት ሌሊቱ፣ አያግደኝም ከመቅረብ ፊቱ። ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ክብር እያበዛሁ አስደስተዋለሁ፣ ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ድምጼን እያሰማሁ አስደስተዋለሁ።

አፌን በምሥጋና ሞልተኸዋልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) እናገር የምችለውን ይህን ነውና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) ያዘነ በፊትህ አይገኝምና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) በፊትህ ቃል ደስታ ይጠግባልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x)

አዝ በማለዳ ምሥጋናዬን አበዛለሁ፣ በቀትርም ሌላ ክብር እጨምራለሁ። ጊዜው መምሸቱ ውድቅት ሌሊቱ፣ አያግደኝም ከመቅረብ ፊቱ። ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ክብር እያበዛሁ አስደስተዋለሁ፣ ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ድምጼን እያሰማሁ አስደስተዋለሁ።

የጐበጠው ሁሉ ቀና ይላልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) ለሰው የማይቻል ይቻልሃልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) ለቃልህ የማይታዘዝ አንድም የለምና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) ብቻህን ተዓምራት ታደርጋለህና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x)

አዝ በማለዳ ምሥጋናዬን አበዛለሁ፣ በቀትርም ሌላ ክብር እጨምራለሁ። ጊዜው መምሸቱ ውድቅት ሌሊቱ፣ አያግደኝም ከመቅረብ ፊቱ። ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ክብር እያበዛሁ አስደስተዋለሁ፣ ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ድምጼን እያሰማሁ አስደስተዋለሁ።

ሕዝብህ ወደ እረፍት ይገባልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) እርዳታህም ከላይ ይመጣልና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) በሰንበትም ችግር አይገኝምና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ (፪x) ሁሉ በሚያርፍበት ትሰራለህና፣ እግዚአብሔር እኔ ልባርክህ። (፪x)

አዝ በማለዳ ምሥጋናዬን አበዛለሁ፣ በቀጥትርም ሌላ ክብር እጨምራለሁ፣ ጊዜው መምሸቱ ውድቅት ሌሊቱ፣ አያግደኝም ከመቅረብ ፊቱ፣ ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ክብር እያበዛሁ አስደስተዋለሁ፣ ሥሙን ልባርከው ሁሌ ጠራዋለሁ፣ ድምጼን እያሰማሁ አስደስተዋለሁ።