ምክር (Meker) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

ከጉብዝናህ ፡ ሚስትህ ፡ ጋር ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ አዎ ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ውደዳት ፡ አፍቅራት ፡ እርሷን ፡ እንደራስህ
እህትህም ፡ ሚስትህም ፡ ባልንጀራህም ፡ ነች
እረዳትህ ፡ ሆና ፡ ለአንተ ፡ የተሰጠች (፪x)

በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው
ከእግዚአብሔርም ፡ ዘንድ ፡ ሞገስ ፡ ከተሰጠ
እያመሰገነ ፡ ስለዚህ ፡ ስጦታ
ቤቱን ፡ በጽድቅ ፡ ይምራ ፡ ይንከባከባታል (፪x)

አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x)
እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ
እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ
ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል
ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x)

አስተዋይ ፡ ሚስት ፡ ግን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ናት
በእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ላይ ፡ እንደተባለላት
ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ እንደምትገዢ
ለባልሽም ፡ ደግሞ ፡ እንዲሁ ፡ ተገዢ (፪x)

ልባም ፡ ሴት ፡ ለባሏ ፡ ዘውድ ፡ እንደምትሆነው
ክብሩ ፡ የት ፡ እንዳለ ፡ ቃሉ ፡ ካጸደቀው
ማፈሪያህ ፡ እንዳይሆን ፡ አንቺም ፡ እንዲህ ፡ ሁኚ
ግን ፡ ልባምነትን ፡ ከቃሉ ፡ አግኚ (፪x)

አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x)
እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ
እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ
ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል
ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x)

የብልህ ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ክርስቶስ ፡ ራስ ፡ ሆኖ
ዐይንም ፡ በእርሱ ፡ አድርጐ ፡ በስሙ ፡ ተማምኖ
መንገዱን ፡ ዝለቁት ፡ የኑሮን ፡ ጐዳና
ግልጽ ፡ ሁኑ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ተከባበሩና (፪x)

ዕውቀትን ፡ እንደዘውድ ፡ በላያቹህ ፡ ጫኑ
ጥበብን ፡ እንዳትዉ ፡ ሞኞች ፡ እንዳትሆኑ
በፍቅር ፡ ለጸና ፡ ለተቻቻለ ፡ ሰው
ጋብቻ ፡ ክቡር ፡ ነው ፡ መኝታው ፡ ንጹህ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ
በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x)
እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ
እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ
ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል
ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x)

እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x)