የዜማ ፡ ጊዜ (Yeziema Gizie) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Eyerusalem Negiya 2.jpg


(2)

ቀን ፡ ሳለ
(Qen Sale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ዘሩን ፡ ከእምባው ፡ ጋር ፡ የዘራ
እርኮ ፡ ተወስዶ ፡ የፈራ
ማሲንቆን ፡ አፍሮ ፡ የደበቀ
ጠላቱ ፡ ወድቆ ፡ ደቀቀ

ቡቃያ ፡ ደርሶ ፡ አፈራ
ወይኑ ፡ ዘለላው ፡ ጐመራ
በደስታ ፡ ነዶውን ፡ አጨደ
ማሲንቆውን ፡ አወረደ

አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ
ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ አሄ ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ዳርቻዬን ፡ አሰፋልኝ ፡ ካዝማዬንም ፡ አጸናልኝ
ይሄው ፡ ቆመዋል ፡ አግሮቼ ፡ ምርኩዝ ፡ ሆኖልኝ ፡ አባቴ
ተሰብሯል ፡ የሃፍረት ፡ ቀንበሬ ፡ ሞልቶታል ፡ አፌን ፡ ዝማሬ
ሞገስ ፡ በረከት ፡ ከደጅ ፡ ገብቷል ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ

አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ
ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ
አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ
ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ

አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ
በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ
ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ
ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ

በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ
በምሥጋና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና

ልቤ ፡ በሃሴት ፡ በደስታ
ፈሰሰ ፡ ቀኔ ፡ ዕልልታ
ከአለት ፡ እቃቃት ፡ ወጥቼ
ድምጼን ፡ ላሰማ ፡ ለአምላኬ

ጭጋጉ ፡ ይሄው ፡ ገፈፈ
ሀዘን ፡ ትካዜው ፡ አለፈ
ላሞግሰው ፡ እንደገና
በድል፡ ዝማሬ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ
ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ
አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ
ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ

አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ
በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ
ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ
ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ

በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ
በምሥጋና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና
በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ
በምሥጋንና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና