አስታዋሼ (Astawashie) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ሰው ፡ የረሳኝን ፡ አስታወስከኝ
ከአመድ ፡ ከትቢያ ፡ ያነሳኀኝ
እኔም ፡ ስላየሁ ፡ ክንድህን
ጌታ ፡ ደራሽ ፡ ነህ ፡ ልበልህ (፪x)

(ደራሽ ፡ ነህ) ምድረ ፡ በዳውን ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) ያሳለፍከኝ
(ደራሽ ፡ ነህ) ምንጭን ፡ አፍልቀህ ፡ አጠጣኀኝ
(ደራሽ ፡ ነህ) አንዴ ፡ ጠጥቼ ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) እንዳልጠማ
(ደራሽ ፡ ነህ) ሕይወት ፡ ሆንክልኝ ፡ በሞት ፡ ከተማ
(ደራሽ ፡ ነህ) ጌታ ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) ለእኔ
(ደራሽ ፡ ነህ) ውዴ ፤ ደራሽ ፡ ነህ ፡ ለእኔ

ቃል ፡ ሲወጣ ፡ ከሰማይ ፡ ማን ፡ ይቆማል ፡ ደጃፉ ፡ ላይ
(ማን ፡ ይቆማል ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ይቆማል ፡ ደጃፉ ፡ ላይ)
በአንዲት ፡ ጀምበር ፡ ደረስክና ፡ አፌን ፡ ሞላህ ፡ በምሥጋና
(ማን ፡ ይቆማል ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ይቆማል)
እንዳለፈው ፡ ታለፈ ፡ አበሳዬ ፡ ተረሳ
(ማን ፡ ይቆማል ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ይቆማል ፡ ደጃፉ ፡ ላይ)
እኔም ፡ ዛሬ ፡ ወግ ፡ ደረሰኝ ፡ የአስታዋሼን ፡ ስሙን ፡ ላንሳ
(ማን ፡ ይቆማል ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ይቆማል)

አዝ፦ አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ ኧረኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ
አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ (፪x)

ሰው ፡ የረሳኝን ፡ አስታወስከኝ
ከአመድ ፡ ከትቢያ ፡ ያነሳኀኝ
እኔም ፡ ስላየሁ ፡ ክንድህን
ጌታ ፡ ደራሽ ፡ ነህ ፡ ልበልህ (፪x)

(ደራሽ ፡ ነህ) ምድረ ፡ በዳውን ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) ያሳለፍከኝ
(ደራሽ ፡ ነህ) ምንጭን ፡ አፍልቀህ ፡ አጠጣኀኝ
(ደራሽ ፡ ነህ) አንዴ ፡ ጠጥቼ ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) እንዳልጠማ
(ደራሽ ፡ ነህ) ሕይወት ፡ ሆንክልኝ ፡ በሞት ፡ ከተማ
(ደራሽ ፡ ነህ) ጌታ ፤ (ደራሽ ፡ ነህ) ለእኔ
(ደራሽ ፡ ነህ) ውዴ ፤ ደራሽ ፡ ነህ ፡ ለእኔ

ኢየሱሴ ፡ ባታየኝ ፡ ማን ፡ ነበረ ፡ የሚያየኝ
(ማን ፡ ነበረ ፡ ቆይ ፡ ማን ፡ ነበረ ፡ የሚያየኝ)
ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ስንገላታ ፡ ደረስክልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
(ማን ፡ ነበረ ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ነበረ)
እነዛ ፡ እጆች ፡ ይባረኩ ፡ እኔን ፡ አቅፈው ፡ ያሳደጉ
(ማን ፡ ነበረ ፡ ቆይ ፡ ማን ፡ ነበረ ፡ የሚያየኝ)
አደረግከኝ ፡ ሽቅርቅር ፡ ጠላት ፡ ይፈር ፡ ያቀርቅር
(ማን ፡ ነበረ ፡ ሄ ፡ ማን ፡ ነበረ)

አዝ፦ አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ
አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ (፪x)

እንዴት ፡ አስታወስከው ፡ ያንን ፡ ሰው (፪x)
እንዴት ፡ አስታወስከው ፡ ያንን ፡ ሰው (፪x)
እንዴት ፡ አስታወስከው ፡ ያንን ፡ ሰው (፪x)
እንዴት ፡ አስታወስከው ፡ ያንን ፡ ሰው (፪x)

አዝ፦ አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ ኧረኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ
አስታዋሼ ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ሰው ፡ ሲረሳኝ ፡ አሰብከኛ (፪x)