Endalkachew Hawaz/Mesganawen Alresawem/Kef Bel

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከጥንት እንደሰማሁት በዓይኖቼም ደግሞ እንዳየሁት አምላክ ከአንተ በቀር የለም መቼም ቢሆን አይገኝም

በምድር ሆነ በሠማይ በየብስ ሆነ በባሕር ላይ በሰው ልጆችም መካከል የለም አንተን የሚስተካከል

አዝ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፬x)

አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (፪x)

ሰዎች የሚያመልኳቸው ዛሬም የሚከተሏቸው ብዙ አማልክት ቢኖሩም አንዳቸውም እውነት አይደሉም

ታላቅ ገናና ኃይለኛ (ገናና ኃይለኛ) ታጋሽ መሃሪ የሆንህ ከጥንት ከጥንትም ጀምሮ (ጀምሮ) በእውነት እግዚአብሔር አምላክ ነህ

አዝ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፬x)

አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (፪x)

በእኔ ላይ ተሹመሃል ፍቅርህ ልቤን ወርሶታል እውነት በርታልኛለች ነፍሴም አምላኳን አውቃለች

ውዴ አንተ የእኔ ነህ እኔም የአንተ ሆኛለሁ በቀረልኝ ዘመን ሁሉ ሳደንቅህ ሳከብርህ ኖራለሁ

አዝ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (፰x)