ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ (Nefsie Tewat Mata) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 3.jpg


(3)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
(Egziabhier Teleq New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

 
ታስተማምናለህ ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ ታመንኩብህ
ታስተማምናለህ ፡ ብቻህን ፡ እኔን ፡ ተደገፍኩብህ (፪x)
ታምኜብሃለሁ ፡ ተደግፌሃለሁ
ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ በአንተ ፡ እመካለሁ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች
በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x)

ለምን ፡ እንደምኖር ፡ አውቃለሁ ፡ አንተን ፡ ስላገኘሁ
ለሕይወቴ ፡ ትርጉምን ፡ ሰጥተሃል ፡ ልቤን ፡ አሳርፈሃል
አርፌብሃለሁ ፡ ረክቼብሃለሁ
ከቤትህ ፡ ጠል ፡ ጠጥቼ ፡ እኔስ ፡ እፎይ ፡ ብያለሁ
(፪x)

እግሮቼ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ቆመዋል
እኔ ፡ አልናወጥም
አረማመዴም ፡ ጸንቶልናል ፡ መሰረቴ ፡ አይወድቅም
የማዕዘን ፡ ድንጋይ ፡ የሕይወቴ ፡ እራስ
ብቃቴም ፡ ጉልበቴም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
(፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች
በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x)