ዘላለማዊ (Zelalemawi) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 5.jpg


(5)

ዘላለማዊ
(Zelalemawi)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:30
ጸሐፊ (Writer): ታምራት ክፍሌ
(Tamerak Kifle)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

አዝ፡- አቤቱ፡ለቀዳሚነትህ፡ጥንት፡ለኋለኛነትህ፡ፍጻሜ፡የለህ (2×) አንተ እግዚአብሔር፡ነህ(4×)፡
አልፋ፡ኦሜጋ፡ፊተኛ፡ኋለኛ(4×)
 1፡-ጌታ፡ዘመናትህ፡ዓመታትህ፡ቢቆጠሩ፡አያልቁ፡ ላንተ፡ምን፡ቢበዙ፡የዕድሜ፡ገደብ፡ከቶ፡አችሉም፡ሊሰጡ፡ ዘመናትን፡አሳልፈህ፡አሳልፈህ፡አንተ፡ብቻ፡ትኖራለህ፡ትኖራለህ፡
        ዘላለማዊ፡ነህ፡(8×)
 2፡-አናልፍም፡ያሉ፡አለፉ፡አንሞትም፡ያሉት፡ሞቱ፡ ኃያላን፡ላንተ፡ሰገዱ፡ኃይል፡የእግዚአብሔር፡ነዉ፡አሉ፡ ያንተ፡አልፋ፡ያንተ፡ኦሜጋ፡ሁሌ፧ጽኑ፡ነዉ፡መሽቶ፡ሲነጋ፡ መንግስትህ፡ቋሚ፡ዘላለማዊ፡ሁሉ፡ሲያከትም፡አንተ፡ነህ፡ነዋሪ፡
        ዘላለማዊ፡ነህ፡(8×)
 ጌታ፡እግኢአብሔር፡ሆይ፡አንተ፡ያልነበርክበት፡ጊዜ፡ ለቅጽበት፡አልነበረም፡አኖርም፡ስልጣንህ፡መንግስትህ፡ነዉ፡ከዘለዓለም(4×)


Navigation menu