ከምድረ ፡ በዳ (Kemedre Beda) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 1.jpg


(1)

የወንጌል ፡ አርበኛ
(Yewengiel Arbegna)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ

የቅባቱ ፡ ውፍረት ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረው (አሃሃ)
የተጫነኝንም ፡ ሸክብ ፡ አወረደው (ኦሆሆ)
እስራቴን ፡ ሁሉ ፡ የፈቱ ፡ እጆቹ
የምለው ፡ የለኝም ፡ በእውነት ፡ ይባረኩ
(፪x)

የጐልያድን ፡ ቁመት ፡ የልብሱን ፡ ክብደት (አሃሃ)
አትኜ ፡ አይደለሁም ፡ የእርሱን ፡ የጦር ፡ ስልት (ኦሆሆ)
ምንም ፡ አይደንቀኝም ፡ ጦሩና ፡ ጡሩሩ
ወድቆ ፡ ይከሰከሳል ፡ በፊት ፡ በግንባሩ
(፪x)

በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ
ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ
አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ
ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ

የረሳኸኝ ፡ መስሎት ፡ ጭፍራውን ፡ ሰብስቦ (አሃሃ)
ውድቀቴን ፡ እንዲያዩ ፡ ወዳጆቹን ፡ ጠርቶ (ኦሆሆ)
ጠአቱን ፡ ቀስሮ ፡ ጉድ ፡ እዩ ፡ ሲላቸው
እኔን ፡ አአሰብክና ፡ ሃፍረት ፡ አለበስከው ፡ እህ
(፪x)

ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ

ፈርጠም ፡ ወፈር ፡ ያለ ፡ እልያብ ፡ እያለ (አሃሃ)
በሰው ፡ የተናቀን ፡ ዳዊት ፡ ይቀብ ፡ ያለ (ኦሆሆ)
መረሳቴን ፡ ሽሮ ፡ በኢየሱስ/በልጁ ፡ ያሰበኝ
ምትክ ፡ የማይኖረው ፡ ለኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
(፪x)

በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ
ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ
አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ
ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ (፪x)