Elias Abte/Yemitesewen Tuafien Alatefam/Hayleh Bedekamie Sigelet

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

𝐁𝐲 𝐀𝐧𝐮 𝐃𝐢𝐫𝐢𝐬𝐞 |ዘማሪ=ኤልያስ ፡ አብጤ |Artist=Elias Abte |ርዕስ=ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ |Title=Hayleh Bedekamie Sigelet |አልበም=የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም |Album=Yemitesewen Tuafien Alatefam |Volume=1 |Track=3 |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic |Lyrics= አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ

በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ
ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ከባርነት ፡ ቤት ፡ ስታላቅቀኝ ቀንበሬን ፡ ሰብረህ ፡ ስትጥልልኝ ባህሩን ፡ በክንድህ ፡ ስትከፍልልኝ ጭቃው ፡ ሳይነካኝ ፡ ስታሻግረኝ ጫማዬ ፡ አልቆ ፡ በእግሬ ፡ ሳልሄድ ጨርቄም ፡ ከገላዬ ፡ ሳይቀደድ በበለዓም ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ለድንኳኔ አጎናጸፍከኝ ፡ ክበር ፡ መድህኔ ንገሥ ፡ መድህኔ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ

በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ
ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ቆሜያለሁ ፡ ሚልን ፡ የሚያፍገመግም ብርቱ ፡ ነኝ ፡ ያለውን ፡ የሚያደክም ይሄ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ፍጹም ፡ ሲያሯሩጥ በወዳጁ ፡ ፊት ፡ ሲያለማምጥ ክረምትም ፡ በጋም ፡ ለማይሞላው ፡ ሆድ ሗላውን ፡ ሳያውቅ ፡ ሰው ፡ ሲካካድ ሁሉን ፡ አራግፋ ፡ ያየችህ ፡ ነፍሴን በድንቅ ፡ አኖርካት ፡ ክበር ፡ ኢየሱሴ ፡ ንገስ ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ

በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ
ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

ጉስቁልናዬን ፡ እያስቆጠረኝ ይሄ ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስለቅሰኝ የቀራዮን ፡ ደም ፡ አንዳልዘነጋ አይኔን ፡ አቅንቼ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ ጉስቁልናዬን ፡ በብልጽግና ከላይ ፡ ከአርያም ፡ ሞላህና ስት ፡ ሸላልመኝ ፡ እፍረት ፡ ሆነለት አበሳውንም ፡ አበዛህበት ጠላቴን ፡ ክበር ፡ የኔ ፡ አባት

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ

በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ
ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

በአንዳንዱ ፡ ቀን ፡ ውስጤን ፡ ሲከፋው የነፍሴን ፡ ጓዳ ፡ ባዶ ፡ ነህ ፡ ሲለው መታጠቂያዬን ፡ ማጥበቅ ፡ ሲያቅተኝ ታናሽነቴ ፡ ሚናቅ ፡ ሲመስለኝ ደመናን ፡ ቀዶ ፡ ክንድህ ፡ ይወርዳል መወርወሪያውን ፡ ይቆራርጣል ሥራዬን ፡ ሰርተህ ፡ ስትዋጋልኝ እጆቼን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አስጫንከኝ ተመስገንልኝ

አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ

በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን
አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ
ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ
ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት
አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ
ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

}}