ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አትዘናጊ (Nefsie Hoy Atezanagi) - ደረጀ ፡ ሙላቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ሙላቱ
(Dereje Mulatu)

Lyrics.jpg


(Volume)

ያልታወቀ ፡ አልበም
(Unknown Album)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ሙላቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Mulatu)

ነቀፋ ፡ ቢበዛ
አጃቢ ፡ ቢታጣ
ያልተጠባበቅነው ፡ መከራ ፡ ቢመጣ
ዕርፉን ፡ ጥለን ፡ አንዴ
ወደ ፡ ሌላም ፡ ሩጫ
የእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ ብቻ
ይሁነን ፡ ማምለጫ
ይህን ፡ ቀን ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ!
አ ት ዘ ና ጊ  !
ቃልኪዳንሽን ፡ ይዘሽ
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ!
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
አንቱ ፡ መባል ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
፪) ዝና ፡ ቢበዛልን ፤ ስማችን ፡ ቢወጣ
ዕልፍ ፡ ገዳይ ፡ ተብሎ ፡ ዘፈንም ፡ ቢመጣ
ሰማይ ፡ ላንቀይር ፡ ማንም ፡ ላይ ፡ ሳንኮራ
በትዕግሥት ፡ እንፈጽም ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ሥራ
አንዴም ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ! አትዘናጊ!
ለቃል ፡ ኪዳንሽ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ!
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ከተማ ፡ መግባት ፡ ሳይመጣ
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?

፫) መውጊያው ፡ ይነሣልን ፡ ብለን ፡ ስንለምነው
ብሎ ፡ የሚመልስልን ፡ ፀጋዬ ፡ በቂ ፡ ነው
እኛም ፡ እንደጳውሎስ ፡ እንኑር ፡ በጽናት
የእግዚአብሔርን ፡ መንግሥት ፡ በግብር ፡ ልንወርሳት
ግድየለም ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ ! አትዘግዪ
ለቃልኪዳንሽ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ!
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?

፬) ዕውነትን ፡ በውሸት ፡ የሚቀላቅሉ
ነጩን ፡ ካድ ፡ አድርገው ፡ ጥቁር ፡ ነው ፡ የሚሉ
ለጥቅም ፡ ያደሩ ፡ ወገኖች ፡ ቢነሡ
እኛ ፡ በታማኝነት ፡ እንኑር ፡ ለንጉሡ
አይደለም ፡ እንዴ ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ! አትዘናጊ!
በፊርማችን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ!
<አዝ ፤ >
ነፍሴ ፡ ሆይ!
ኢየሱስን ፡ ስንቀበል
ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል
ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
አገር ፡ መዞር ፡ ሳይጀመር
ጓዳ ፡ እያለን ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር?
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተገባባነው ፡ ቃልኪዳን ፡ ይከበር!