ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ (Tamagn Sew Tefa) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ
ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ
ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ
በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ
ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ

በእርጅናዬ ፡ ዘመን ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አገኘሁ
አደራ ፡ ማይበላ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ብዙ ፡ ወሰደብኝ ፡ ሚስጢሩ ፡ ሳይገባኝ
ይሄ ፡ ሰው ፡ ማመኔ ፡ ደህና ፡ አድርጐ ፡ ጐዳኝ

የዘመናት ፡ ጥቅልል ፡ የምድር ፡ እና ፡ ሰማይ
የጌታን ፡ መመለስ ፡ በሁለት ፡ ዐይኖቸ ፡ ላይ
ያወኩት ፡ ዛሬ ፡ ስአቱ ፡ መድረሱን
ያበላሁት ፡ ወዳጂ ፡ ሲያፋጭብኝ ፡ ጥርሱን

ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል
ጨዋነትና ፡ ክበር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት
የቃል ፡ አምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት

ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ
ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ
ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ
በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ
ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ

እወየው ፡ ጯዋነት ፡ ሰፈር ፡ ጥሎ ፡ ሄዷል
ወገን ፡ በወገኑ ፡ ያልፍርሃት ፡ ነግዷል
ያስቀመጡት ፡ እቃ ፡ አይገኝም ፡ ዳግም
ሁሉ ፡ ቃል ፡ አጥፊ ፡ መሃላ ፡ ቢያደርግም

ወንድሞቹ ፡ ሸጡት ፡ ዮሴፍን ፡ ለእንጀራ
ማዕድ ፡ የተጋሩት ፡ ሆኑት ፡ ባላጋራ
የጥንት ፡ ታሪክ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ በዚህ ፡ የለም
ብዬ ፡ ነበር ፡ ኋላ ፡ በራሴ ፡ ሊፈጸም

ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል
ጨዋነትና ፡ ክብር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት
የቃል ፡ እምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት


Navigation menu