Dereje Kebede/Collection 2/Cherqehen Yezie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ደረጀ ከበደ ዶ/ር ርዕስ ጨርቅህን ይዤ

አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/

ክላሲካል ድካሜን አውቃለሁ ኃጢያት ሲያሸንፈኝ ያም ቢሆን ጨርቅህን ማንም አያስጥለኝ ማንም አያስጥለኝ የአመፃዬ ክምር ቢያስቆጣህም በጣም አንተው እስክትምረኝ ከቤትህ አልወጣም ከቤትህ አልወጣም

አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/

ክላሲካል ፍሬ አልባ ንሰሃ ነጋ ጠባ ማረኝ በፊትህ እንዳልቆይ እጅግ አሳፈረኝ እጅግ አሳፈረኝ አመጻዬ በዝቶ ጭቃ ባላቁጥም ደጅህ እሞታለሁ ተስፋዬን አልቆርጥም ተስፋዬን አልቆርጥም

አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/

ክላሲካል የነፍሴን ውሳኔ አንተው ታውቀዋለህ እንደምወድህም ውስጤን ታየዋለህ ውስጤን ታየዋለህ ከልጅነት ወራት ጀምሮ አውቅሃለሁ እንዳንተ ቸር ወዳጅ ወዴት አገኛለሁ ወዴት አገኛለሁ

አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/

ክላሲካል ለህይወቴ ሰላም ለልቤ ፀጥታ ዘለአለም ገዥዬ አንተ ብቻ ጌታ አንተ ብቻ ጌታ ግራ ቀኝም አልል ነፍሴንም አልሸጣት ከአንተ ተለይታ አወይ ትርጉም የላት አወይ ትርጉም የላት

አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/ ክላሲካል