ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ (Nefsien Lemot Shechie) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የዓለም ፡ መራቀቅ ፡ እኔን ፡ አይገደኝም
የጠላት ፡ ድንፋታም ፡ አያስጨንቀኝም
አምላኬን ፡ አውቃለሁ ፡ ፍፁም ፡ የለም ፡ ቢሉ
እኔስ ፡ አለ ፡ እላለሁ ፡ ተናግሮኛል ፡ ቃሉ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም
ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም

እኔ ፡ እኔነቴን ፡ እስካላዘዝኩበት
የሚያዝበት ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ ባለንብረት
ይህን ፡ ክቡር ፡ ገላ ፡ በዋዛ ፡ አላየውም
የፈጠረኝንም ፡ አምላኬን ፡ አልክድም

አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም
ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም

ገንዘብ ፡ ነው ፡ ጌጣጌጥ ፡ የትኛው ፡ ነው ፡ ትርፉ
ከአምላክ ፡ ተነጥሎ ፡ በዓለም ፡ ውስጥ ፡ መክነፉ
ሁሉም ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ወደ ፡ አፈር ፡ ከሄደ
ዋጋው ፡ የላቀ ፡ ነው ፡ አምላክን ፡ ያልካደ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም
ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም


Navigation menu