ማንም ፡ አያውቅም (Manem Ayawqem) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ማንም ፡ አያውቅም ፡ ያየሁትን ፡ ችግር
ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በስተቀር
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጭንቀቴን ፡ የሚያውቀው
እረፍት ፡ የሚሰጠኝ

ድካሜንም ፡ ብርታቴንም ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ሃዘኔንም ፡ ጭንቀቴንም ፡ ታውቃለህ

ማንም ፡ አያውቅም ፡ ያየሁትን ፡ ችግር
ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በስተቀር
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጭንቀቴን ፡ የሚያውቀው
እረፍት ፡ የሚሰጠኝ

አንተ ፡ ብቻ ፡ በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ያለኸው
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ምንም ፡ ሳይቀር ፡ ታውቃለህ

አልናገርም ፡ ችግሬንም ፡ ለሰው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ፡ ለአንተ ፡ ነው
ሳልፈራ ፡ ሳላፍር ፡ ችግሬን ፡ በሙሉ
ለአንተ ፡ እናገራለሁ

በመንፈሴ ፡ ስቀዘቅዝ ፡ አምላኬ
ያነቃኛል ፡ ስደነዝዝ ፡ ይመስገን

ማንም ፡ አያውቅም ፡ ያየሁትን ፡ ችግር
ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በስተቀር
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጭንቀቴን ፡ የሚያውቀው
እረፍት ፡ የሚሰጠኝ


Navigation menu