ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው (Gieta Redatie New) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ
መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ
ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው
ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው

ሕይወቴ ፡ ሲደክም ፡ ሲዝልብኝ
ረዳት ፡ የሌለኝ ፡ እኔን ፡ ሲመስለኝ
ጌታ ፡ በክንዶቹ ፡ ያነሳኛል
ደረቁን ፡ ሕይወቴን ፡ ያረካዋል

አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ
መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ
ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው
ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው

አንዴ ፡ በሸለቆ ፡ እንዲያ ፡ ሳለቅስ
አንዴ ፡ በተራራ ፡ ስፈነጥዝ
የመስቀሉን ፡ መንገድ ፡ ስለማመድ
ብዙ ፡ ትምህርት ፡ አለው ፡ ብወድ

አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ
መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ
ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው
ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው

እኔ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም ፡ እቆማለሁ
የሕይወቴን ፡ መንገድ ፡ መርጫለሁ
እደክማለሁ ፡ እንጂ ፡ ከቶ ፡ አልፈራም
የሕይወትን ፡ እራስ ፡ አልክደውም

አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ
መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ
ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው
ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው (፪x)


Navigation menu