እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ (Enien Gieta Hoy) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቃልህን ፡ ለማንበብ ፡ ዓይኔ ፡ ታወረ
እንዳልጸልይ ፡ ጉልበቴ ፡ ታሰረ
አንተን ፡ እንዳላስብ ፡ አዕምሮዬ ፡ ዛለ
እግሬም ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ኮበለለ

እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል
ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል
ወድቄያለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ
እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ

ጠፋሁኝ ፡ ጌታ ፡ ካልደረስክልኝ
ዓለም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ አነከባለለኝ
ከኃጢአት ፡ ባሕር ፡ ልሰምጥ ፡ ነውና
ጌታ ፡ ቆይ ፡ እባክህ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

መች ፡ ጨቀንክ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ በልጅህ
አውቃለሁኝና ፡ ጉድለቴን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ኃጢአቴን ፡ ማረኝ
የምመራበትን ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ

አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ወዲህ ፡ ስመጣ
እኔንም ፡ ከጥፋት ፡ ሊያወጣ
እጁን ፡ ላከልኝ ፡ ፍፁም ፡ አዳነኝ
ከእንግዲህስ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ ነኝ

ፍፁም ፡ ቸል ፡ አልልም ፡ እርሱን ፡ ስከተል
እኔኑን ፡ ለመውሰድ ፡ ስለሚያስብ
መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ቢከብደኝ ፡ እንኳን
ፍፁም ፡ ለመሸከም ፡ አልቦዝንም


Navigation menu