አዎን ፡ ያያል / ያየኛል ፡ ወይ (Awon Yayal) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያየኛል ፡ ወይ ፡ ልቤ ፡ ሲጨነቅ
ለነፍሴ ፡ ሰላም ፡ ስሻ
ሸክም ፡ ሲከብደኝ ፡ ስንገላታ
መንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ስደክም

አዝ፦ አዎን ፡ ያያል ፡ ይረዳኛል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ፈተና ፡ ሲገጥመኝ
ኢየሱስ ፡ ይረዳኛል

ያየኛል ፡ ወይ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም
ፍርሃትም ፡ እኔን ፡ ሲከበኝ
ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ፍፁም ፡ ስደክም
አምላኬ ፡ በቅርብ ፡ አለ ፡ ወይ

አዝ፦ አዎን ፡ ያያል ፡ ይረዳኛል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ፈተና ፡ ሲገጥመኝ
ኢየሱስ ፡ ይረዳኛል

ያየኛል ፡ ወይ ፡ ኃይሌ ፡ ሲከዳኝ
ችግር ፡ ልቋቋም ፡ ሳልችል
ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ እምባዬም ፡ ሲፈስ
አምላኬ ፡ በእርግጥ ፡ አለ ፡ ወይ

አዝ፦ አዎን ፡ ያያል ፡ ይረዳኛል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ፈተና ፡ ሲገጥመኝ
ኢየሱስ ፡ ይረዳኛል (፪x)


Navigation menu