አንድ ፡ ነገር (And Neger) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አንድ ፡ ነገር ፡ በልቤ ፡ ሆነ
ኢየሱስ ፡ ሲያድነኝ (፪x)
ሕይወቴም ፡ በፍቅሩ ፡ ጋለ
ክብር ፡ ክብር ፡ ለስሙ

አምላኬ ፡ በዚያ ፡ መስቀል ፡ ላይ
በቀራኒዮ (፪x)
ለእኔ ፡ መከራውን ፡ አየ
ደሙም ፡ እኔን ፡ አነጻኝ

ግንባርህ ፡ በሾህ ፡ ተበሳ
መራራን ፡ ጠጣ (፪x)
ጐንህም ፡ በጦር ፡ ተወጋ
ስለእኔ ፡ ኃጢአት ፡ ብለህ

የደም ፡ ላብም ፡ አጠለቀህ
በጸሎት ፡ ሜዳ (፪x)
አህዛብም ፡ ቀለዱብህ
መቱህ ፡ ተፉብህ ፡ ጌታ


Navigation menu