Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Wetmedu Tesebere

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ደረጀ ከበደ ርዕስ ወጥመዱ ተሰበረ አልበም አዳኜ ኢየሱስ

አቤቱ የታለ ጠላታችን በነነ ከዓይናችን ከእጁ ተወሰደ መውጊያው ቀስቱ የታመነበቱ

ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)

ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር ለእኛ ቁልቁል እንድንገባ እግዚአብሔር ግን ፈጥኖ ፊት ቀደመ ዲያቢሎስ ሰጠመ

ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)

በቁጥቋጦ መሃል ጠላት ጠምዶ ሊጥለን አሳዶ ሌት ከቀን አደባ ዐይኑን ከፍቶ መና ሊቀር ለፍቶ

ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)

በሰልፍ ያስጨነቀን ብናኝ ሆነ ኃይሉ ተበተነ እንዳረጀ አንበሳ ዝንብ ወረረው ድንፋታው ተለየው።