ሰላም ፡ ወዴት ፡ አለሽ (Selam Wediet Alesh) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አዳኜ ፡ ኢየሱስ
(Adagnie Yesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

በየአመቱ ሲፋረሙ
የብራናው የቀለሙ
እንዲያው ለፉ መካሪ አጡ
ሰላም ውድዋን ከየት ያምጡ

ይህን ቆጥረው ያን ሲፈቱ
ጀምበር ገባች መላም መቱ
ሚስጥሩማ ግልጽ ነበር
ለእግዚአብሄር ሰው ቢሰበር

ሰላም 4x ወዴት አለሽ
እሩቅ አገር 2x ተሸሽገሽ
ያለሽበት ያንቺ ማረፊያ ከቅጥር በስትያ
ሰው ወጥቶ ጥሮ አያገኝሽ እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደትላት ባዶ እጁን ቀረ መና ልፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማመን ጠልቶ
መና ቀረ ልፍቶ መና ቀረ ልፍቶ

የሰላሙን ልኡል ናቁህ
አልፈቅደም ገላመጡህ
አቅማቸውን ያላወቁ
በምድር ገነው የመጠቁ

በሰቅል ወርቅ በእልፍ ሽልንግ
በጥጥ መሬትም ቢያስፈልግ
ከገበያ ሊሸምቶት
በምጡ ነው ወይ ሊወልዶት
ሰላም ስሞን ወተወቶት

ሰላም ሰላም....

ሰላም 4x ያለው
ሀገርዋ ሰማይ ነው ዘርዋ በምድር የለም

ምንጮ በዚህ የለም በሩቅም በቅርቡ