Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Ahadu Elalehugn

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

|Lyrics=::አሃዱ እላለሁ በምስጋና

አፌን እክፍታለሁ በምስጋና
እርሱ ያሰበልኝ በለጠና
የእኔ ከንቱ ሆኖ ቀርቷልና

ወጥቼ ወርጄ ብዙ አስቤአለሁ አውጠንጥኛለሁ ልቤ እሰክሚጨነቅ በስጋ ጉዞ ተክለፍልፌአለሁ ኋላ ግን በየሱስ ተሰብስቤያለሁ /፪

ፈቃዱን አውቄ በምስጋና ቃል ስሙን ጠርቼ
እውነተኛ ድምፁን ከአንደበቱ ጠርቶኝ ስምቼ
እርሱን እጠብቃለሁ ሌላውን ትቼ /፪

በከንቱ ነበረ መደካከሜ ላይ ታች ማለቴ ነገ ዛሬ እንዲሆን በምኞት ሩጫ እጅግ መትጋቴ አሁን ግን ልቀበል ከላይ ካባቴ /፪

እንግዲህ ካገኘሁ አጋዥ ከአርያም ሐሳቤን ጠቅላይ
ደቂቃም አታልፍም አይኔን አንስቼ ወደላይ ሳላይ
ድል ይላክልኛል ከሩቅ ከሰማይ /፪

}}