Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Amesegenalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ አመሰግናለሁ አልበም የሰው እጅ የሌለበት

አመሰግናለሁ እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ ነውና ሁሉን ይሁን ያለ ውብ አሮጐ የሰራው እርሱ ነውና ብቻውን የሚኖር በታላቅ ብርሃን ሰው በማይቀርበው የፍጥረት መሰረት ተቆጣጣሪ ሁሉ በእጁ ነው (፪x)

ላመስግነው ቆሜ እንደገና ጥበብ ኃይልም የእርሱ ነውና ከንፈሮቼ ለእርሱ ይዘምሩ እስትንፋሴም ይሁን ለክብሩ (፪x)

የእግዚአብሔር ቸርነት ምህረቱ ከቦኝ ነው ዛሬ ላይ መቆሜ አሄ ትንፋሼን መንገዴን በእጆቹ የያዘው ሆኖልኝ አቅሜ ኤሄ ወራት ተቆጠሩ አመታት አለፉ ዛሬም ዘምራለሁ አሄ በሕይወት እንድኖር ስለፈቀደልኝ አመሰግናለሁ ሆሆ

አቤት አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት የእግዚአብሔር ምህረት አቆመኝ እኔም ልስገድለት እጄን ይዞኝ አምላኬ ወዶኛል ጌታ ራርቶልኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል (፬x)

አመጸኛው ጠላት ከሚወረውረው ጦር እያስመለጠኝ አሄ ቀስት እየሰበረ እሳት እያጠፋ በእጁ እየከለለኝ ሆሆ ከአቻምናን አልፌ አምናንም አልፌ ይሄው በሕይወት አለሁ አሄ ቀሪውን ዘመኔን እንዲባርክልኝ ጌታን አምነዋለሁ ሆሆ

አቤት አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት የእግዚአብሔር ምህረት አቆመኝ እኔም ልስገድለት እጄን ይዞኝ አምላኬ ወዶኛል ጌታ ራርቶልኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል (፬x)

የእግዚአብሔር ደግነት በምን ይመዘናል መለኪያስ አለው ዎይ አሄ ከጨለማው ዓለም አንድ ልጁን ሰጥቶ ታድጐኝ የለም ዎይ ሆሆ ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሴ መድሃኒት የዓለሙ ቤዛ አሄ በእርሱ ተመርጬ በደሙ ነጽቼ ቀረልኝ አበሳ ሆሆ

አቤት አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት የእግዚአብሔር ምህረት አቆመኝ እኔም ልስገድለት እጄን ይዞኝ አምላኬ ወዶኛል ጌታ ራርቶልኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል (፬x)

እንግዲስ እርምጃዬ የማስተዋል ይሁን ጌታ የሚከብርበት የምድር ላይ ኑሮዬን በትዕግሥት ሮጬ የምጨርስበት በቀንም በማታም አምላኬን የመፍራት ጥበብ ይሁንልኝ የሮጥኩት ሩጫ በእሳት ስፈተን አይቃጠልብኝ ቀኑ ደርሶ በዐይኔ እስካየው ድረስ የነፍሴን መድሃኒት ልገዛ በውነት ልስገድለት ውዱ ጌታ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ (፪x) ከፍ ይበል ለዘለዓለም ለዘለዓለም ይንገሥ።