አልረሳውም (Alresawum) - ዳንኤል አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 6.jpg


(6)

የሰው እጅ የሌለበት
(Yesew Ej Yelielebet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

 
ጌታ በሕይወቴ ወዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም
እርሱ በሕይወቴ ፈቅዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም

አልረሳውም ያደረገልኝን
አልረሳውም ለእኔ የሆነልኝን
አልረሳውም የአምላኬን ውለታ
ዘወትር ልቀኝ ለሚያኖረኝ በደስታ

ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ
አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ
ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው
ያኔ በመከራ የደገፈኝ
ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ
የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው (፪x)

ይሁን ያለው ሁሉ ይሆናል
ሃሳቡን ማን ይከለክላል
እንዴት ልርሳ መልካምነቱን
ልዘምር እንጂ ምህረቱን

ተስፋ ላጣ ተስፋ ነው ለምስኪኑ
ወላጅ ላጣ ብቸኛ ነው ወገኑ
ላመስግነው እንጂ እኔ ልወድሰው
ኃይሌ ክብሬ ታሪኬም ኢየሱስ ነው

ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ
አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ
ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው
ያኔ በመከራ የደገፈኝ
ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ
የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው

ዮሴፍን ከእስር ቤት ያወጣ
ለሹመት ሽልማት ያበቃ
የዳንኤል አምላክ ተዐምረኛ
ከአንበሶኝ የሚያድን ከበላተኛ

አይገርምም ወይ ይሞታል የተባለው
ሕይወት ዘርቶ በግሩ ቆሞ አየነው
የቀመሰ ያውቀዋል የእርሱን ማዳን
የተነካ በእግዚአብሔር ብርሃን

ጌታ በሕይወቴ ወዶ ያደረገውን መቼም አልረሳው
እርሱ በህይወቴ ፈቅዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም

አልረሳውም ያደረገልኝ
አልረሳውም ለእኔ የሆነልኝን
አልረሳውም የአምላኬን ውለታ
ዘወትር ልቀኝ ለሚያኖረኝ በደስት