Daniel Amdemichael/Yehonal/Yehonegn Tela

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በምድረ በዳ የሆነኝ ጥላ ያኔ የተሸከመኝ ሆኖኝ ከለላ (፪x) ዛሬም ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው ጊዜና ሁኔታ የማይለውጠው (፪x)

ጌታ ነው ጌታ ዛሬም ጌታ ጌታ ነው ጌታ ነገም ጌታ (፪x)

አዝ ነፍሴ በጌታ ሃሴት አደረገች በጌታ ሃሴት አደረገች ዛሬም ብድራቱን እያሰበች ብድራቱን እያሰበች (፪x)

በእርሱ ቸርነት አምናን አልፌ በበረታው ክንድ ላይ ተደግፌ (፪x) ዛሬ ደስ ብሎኝ እዘምራለሁ የሠማይን አምላክ አመልከዋለሁ (፪x)

ሃዘኔ ጠፍቶ በደስታ እዘምራለሁ ለዚህ ጌታ ሞገስ ለአምላኬ ክብር ይሁን ልሰዋ ዜማ ያማረውን

አዝ ነፍሴ በጌታ ሃሴት አደረገች በጌታ ሃሴት አደረገች ዛሬም ብድራቱን እያሰበች ብድራቱን እያሰበች (፪x)

ድል አስለምዶኛል ጠላትን ማሸነፍ ረግጬው አልፋለሁ ሺህ ጦር ቢሰለፍ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ ስልጣንን የሰጠኝ አሸናፊው ጌታ አሸናፊ ያረገኝ

ዘመን መጣ መጣ የዜማ ወራቱ ኢየሱስ የሚከብርበት ሲመለክ በቤቱ ያማረ ዝማሬ ቅኔዉም ለእርሱ ነው የይሁዳ አንበሳ መታመኛዬ ነው መታመኛዬ ነው (፪x) መደገፊያ ነው (፪x)

ድል አስለምዶኛል ጠላትን ማሸነፍ ረግጬው አልፋለሁ ሺህ ጦር ቢሰለፍ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ ስልጣንን የሰጠኝ አሸናፊው ጌታ አሸናፊ ያረገኝ

ዘመን መጣ መጣ የዜማ ወራቱ ኢየሱስ የሚከብርበት ሲመለክ በቤቱ ያማረ ዝማሬ ቅኔዉም ለእርሱ ነው የይሁዳ አንበሳ መታመኛዬ ነው

መታመኛዬ ነው (፪x) መደገፊያ ነው (፪x) መታመኛዬ ነው (፪x) መደገፊያ ነው (፪x)