Daniel Amdemichael/Yehonal/Oho Yeredagnen

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ
ኦሆ የረዳኝን አመሰግናለሁ
በጉባኤው መሃል ከፍ አደርገዋለሁ
እኔንም ረድቶኛል በእውነት የምትሉ
እስኪ ዘምሩለት ለእርሱ እልል በሉ
እልል በሉ አሃሃ ዘምሩለት አሃሃ
ለድል ጌታ የድል መዝሙር ተቀኙለት
ክብር ለእርሱ ኦሆሆ ሞገስ ለእርሱ ኦሆሆ
ለወደደን ላፈቀረን ለንጉሡ

እንደ እኔማ ቢሆን እንደበዛው ኃጢያቴ
በፊቱ ባልተገኘሁ ባይራራልኝ አባቴ
ምህረቱ ለእኔ በዛስ ቸርነት አደረገልኝ
አቤቱ መድሃኒቴ ይክበር ይመስገንልኝ (፬x)

አዝ
ኦሆ የረዳኝን አመሰግናለሁ
በጉባኤው መሃል ከፍ አደርገዋለሁ
እኔንም ረድቶኛል በእውነት የምትሉ
እስኪ ዘምሩለት ለእርሱ እልል በሉ
እልል በሉ አሃሃ ዘምሩለት አሃሃ
ለድል ጌታ የድል መዝሙር ተቀኙለት
ክብር ለእርሱ ኦሆሆ ሞገስ ለእርሱ ኦሆሆ
ለወደደን ላፈቀረን ለንጉሡ

የውስጤን የልቤን ነግሬው ነበር
ፀሎቴን መልሶልኝ ጠላቴን አሳፈረ
ጉልበቴን አፀናልኝ ረዳኝ መድሃኒቴ
ድንቁን እዘምራለሁ
ያደረገውን በሕይወቴ የሰራውን በሕይወቴ (፫x)

አዝ
ኦሆ የረዳኝን አመሰግናለሁ
በጉባኤው መሃል ከፍ አደርገዋለሁ
እኔንም ረድቶኛል በእውነት የምትሉ
እስኪ ዘምሩለት ለእርሱ እልል በሉ
እልል በሉ አሃሃ ዘምሩለት አሃሃ
ለድል ጌታ የድል መዝሙር ተቀኙለት
ክብር ለእርሱ ኦሆሆ ሞገስ ለእርሱ ኦሆሆ
ለወደደን ላፈቀረን ለንጉሡ

የታሰርኩበት ገመዴን በጥሶ
የጠላቶቼን ሰፈር መንደሩን አፈራርሶ
እንደ አንበሳ ደቦል ጀግንነት ሞልቶኛል
በጠላቶቼ ራስ ላይ አቁሞ ያዘምረኛል (፲፪x)