Daniel Amdemichael/Yehonal/Meheret Yebezalet

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ ምህረት የበዛለት አልበም ይሆናል

አዝ አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x) አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x) ያመስግን እንጂ ኦሆ ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x) ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)

መኖሬን መኖር ላሳኛኸው አይበቃም ይህ ብቻ አውቃለሁ ሺህ አንደበት ኖሮኝ ምነው ስላንተ ዘምሬ ብዘልቀው

አንደበት ያለው ሁሉ ማዳንህን ይናገረው ምሕረት ፀጋ የበዛለት ክቡር ሥምህን ከፍ ያድርገው ያመስግነው (፪x)

ከአማልክት መሃል አንተ ብቻህን ጌታ ነህ አንተ ብቻህን አምላክ ነህ

አዝ አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x) አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x) ያመስግን እንጂ ኦሆ ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x) ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)

አቤቱ ጌታ አምላክ ሆይ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ (፪x) ክብርህን ኃይልህን አይ ዘንድ ይሄ ለእኔ ጥማቴ ነው (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ልበል ሥምህን ላክብረው የአንተ መክበር ለእኔ ደስታ ነው